በቅርቡ ህይወቷን በመኪና አደጋ ያጣችው የተዋናይት ሰብለ ተፈራ ባለቤት አቶ ሞገስ ተስፋዬ የወንጀል ክስ ተመሰረተበት፡፡
የፌደራል አቃቤ ህግ በ09/02/08 ፅፎ ያወጣበት የክስ ማመልከቻ እንደሚያሳየው አቶ ሞገስ ኮድ 2- አ.አ የሆነች መኪና ይዞ ከላንቻ ወደ ሳሪስ አቅጣጫ እያሽከረከረ ንፋስ ስልክ ቀለም ፋብሪካ ሲደርስ ፍጥነቱን ተቆጣጥሮ በሁለት እጁ መሪ ይዞ ፊትለፊቱን እያየ ማሽከርከር ሲገባው መሪውን በአንድ እጁ በመያዝ በአንድ እጁ ጎንበስ ብሎ ሬዲዮ እየጎረጎረ ከፊት ለፊቱ ከነበረው ኮድ 3- ኢት ታርጋ ያለው ተሳቢ ጋር በመጋጨቱ አብራው ተሳፍራ የነበረችውን ሰብለ ተፈራ ከፍተኛ የጭንቅላትና የአንጎል ጉዳት ደርሶባት ህይወቷ እንዲያልፍ በማድረጉ በፈፀመው በቸልተኝነት ሰው መግደል ወንጀል ተከሷል፡፡
በተጨማሪም አቃቤ ህግ በተሳቢው ላይ የ100 ብር የንብረት ጉዳት በማድረሱም ሁለተኛ ክስ ፅፎበታል፡፡ አደጋው የደረሰው በሰብለ ስም በተመዘገበች ብርማ ቀለም ያላት የ2000 ቪትስ ሞዴል መኪና ሲሆን መኪናዋ 997 የሞተር ሲሲ/ችሎታ/ እና 45 የፈረስ ጉልበት አላት፡፡ አቶ ሞገስ ፍርድ ቤት ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ Source ( Ethiopia Prosperous))
0 comments:
Post a Comment