Sunday, August 16, 2015

ኣቶ ሬድዋን ሁሴን ከዲያስፖራ የሶሻል ሚዲያ ኣባላት ጋር ውይይት ኣደረጉ::


በሚዲያ ስራ ላይ የተሰማሩ የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ከመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች /ቤት ሚኒስትር ከክቡር አቶ ረድዋን ሁሴን በሀገረ ገጽታ ግንባታ ዙሪያ የጋራ ውይይት አደረጉ::

የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች /ቤት ሚኒስትር ክቡር አቶ ረድዋን ሁሴን በሚዲያ ስራ ላይ የተሰማሩ የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በጽቤታቸው ተቀብለው ባደረጉት ውይይት መንግስት እያከናወነ ያለው የልማትና የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ስራዎች በተሰራው ልክ በቂ የሚዲያና የኮሙዩኒኬሽን ስራ ሽፋን አግኝቷል ማለት አይቻልም። ይህንን ችግር ለመፍታት በመንግስት በኩል የኮሙዩኒኬሽንና ሚዲያ ባለሙያውን አቅም በማሳደግ ለህብረተሰቡ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል ስራ እየተሰራ ሲሆን በተለይ በኮሙዩኒኬሽን ዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎች በየተቋማቸ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች በተለያዩ ሚዲያዎች ለህብረተሰቡ መረጃ ተደራሽ እንዲያደርጉ የሚያስችል መመሪያ በማውረድ በየተቋሙ ተግባራዊ እንዲሆን ጥረት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል


እንዲሁም መንግስት የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ፖሊሲዎችን አውጥቶ ከባለድርሻ አካለት ጋር ውይይት እያደረገ ሲሆን ፖሊሲው በሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶች ባለሙያዎች በጋራ የሚያሰራና የሀገሪቱን ገጽታ ግንባታ ስራ በተናበበና በተቀናጀ ሁኔታ ለመምራት የሚያስችል ነው ብለዋል።
የዲያስፖራ ማህበረሰቡም ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የሚያስችል የጋራ የሆነ አሰራር ስለሌለን በሀገሪቱ እየተከናወኑ ያሉ የልማትና የዲሞክራሲ ስራዎች በአግባቡ ለውጭው ማህበረሰብ እያደረስን አየደለም ሰለሆነም ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ የምናገኝበት አሰራር እንዲዘረጋልን እንፈልጋለን ብለዋል።
ክቡር ሚኒስትሩም እንዳሉት የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ፖሊሲው ውይይቱ አልቆ ሲጸድቅ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭው የሚገኙ ሚዲያዎች ወጥ የሆነ የመረጃ ቅብብሎሽ ስርዓት እንዲኖር የሚያስችል አሰራር እንዘረጋለን እንዲሁም ወቅታዊ መረጃዎችን በጽ/ቤቱ ዌብ ፖርታል እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያ እንዲደርሳችሁ የምናደርግ ሲሆን በተለይ አጫጭር ዶክመንተሪዎች 5-7 ደቂቃ የሚሆኑ ደክመንትሪዎች ለሚዲያ ግብዓት በሚሆን መንገድ ለመስራት የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን በወቅቱ እንዲደርሳቹ ይደረጋል። የሚያጋጥማችሁን ችግሮች በጋራ ተቀራርበን በመስራት የምንፈታቸው ሲሆን ለኢትዮጵያውያንም እና ለውጭው ማህበረሰብ በሀገራችን እየተከናወኑ ያሉ የልማትና የዲሞክራሲ ስራዎች የማስተዋወቅ ስራ በጋራ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።  Source (Government Communication Affairs Office). 

0 comments:

Post a Comment