Wednesday, August 26, 2015

በመተካካት ተሸኝተው የነበሩት የሕወሓት ነባር አመራሮች ተመለሱ::(Up dated )
ይሁን እንጂ እንደ  ኤ ፍ ቢ ሲ  ዘገባ  አቶ አባይ ጸሃዬ፣ አቶ ቴዎድሮስ ሀጎስ፣ አቶ አባዲ ዘሙ፣ አቶ ጸጋዬ በርሄ፣ ወይዘሮ ሮማን ገብረስላሴ፣  አቶ ተወልደ በርኸ እና አቶ ተክለወይን አሰፋን ከህወሃት ማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት በክብር እንዲሰናበቱ ተደርጓል። ከዚ ህም በተጨማሪ  

   ኣቶ ኣዲሱ ለገሰንና  ኣቶ ዮሴፍ ረታን ደህዴን ዶክተር ካሱ ኢላላን ከማአከላዊ ኮሚቴ  ኣባልነታቸው በክብር  ኣሰናብ ቷቸዋል:: 

ከነሐሴ 16 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ በመቐለ ሰማዕታት አዳራሽ እየተደረገ ባለው 12ኛው የሕወሓት ጉባዔ፣ በመተካካት ተሸኝተው የነበሩ የሕወሓት አመራሮች በጉባዔው እንዲመረጡና እንዲመርጡ ተወሰነ፡፡ አዘጋጅ ኮሚቴው የጋበዛቸው ያለ ድምፅ እንዲሳተፉ ነበር፡፡ ከ1,650 በላይ ጉባዔተኞች በታደሙበት ጉባዔ የተገኙ አንድ ተሳታፊ ከዚህ ቀደም ተገፍተው የወጡ ያሏቸው ነበር አመራሮች በድምፅ እንዲሳተፉ ጥያቄ ካቀረቡ በኋላ፣ በጉዳዩ ላይ የመከረው ጉባዔ በጭብጨባ በሙሉ ድምፅ ጥያቄውን ተቀብሎታል፡፡ በዚህም መሠረት ዶ/ር አርከበ እቁባይ፣ አቶ ስብሃት ነጋ (አቦይ)፣አምባሳደር ሥዩም መስፍን፣ አምባሳደር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ፣ አቶ ፀጋዬ በርኼን ጨምሮ 17 ነባር አባላት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ጉባዔው በእስካሁኑ ቆይታው በአንደኛው የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ፣ በመልካም አስተዳደርና በመተካካት ላይ ተወያይቷል፡፡ በመልካም አስተዳደር እጦት ክልሉ እየተጠቃ እንደሆነ በርካታ አስተያየቶች ተሰጥተዋል፡፡ በተለይ በአንድ የሃይማኖት አባት የቀረበው የመልካም አስተዳደር እጦት ትኩረት የሳበ ነበር፡፡ የሕወሓት አመራሮች ድርጅቱ ቀድሞ አንግተውት የነበረውን ዓላማ እንደረሱ በአጽንኦት ገልጸው፣ ፍትሕ በገንዘብ እየተገዛ የክልሉ ሕዝብ የማያውቀው አዲስ ባህል በመጎልበቱ ይህንንም እንደሚዋጉት አመልክተዋል፡፡ ‹‹እሳት ያልፈራ ሕዝብ እናንተን የሚፈራ ይመስላችኋል?›› ሲሉም ጥያቄአቸውን አቅርበዋል፡፡ መተካካትን በተመለከተም ወደ መገፋፋት በመቀየሩ ያለ ዕድሜና አቅም ማነስ ዶ/ር አርከበና አምባሳደር ብርሃነ እንዲወጡ መደረጉን ተችተዋል፡፡ እንደ ድሮው መገማገምና አንዱ አንዱን ተጠያቂ ማድረግ በመሸፋፈንና በመጠባበቅ መቀየሩም ተገልጿል፡፡

የሕወሓት ሊቀመንበርና የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ዓባይ ወልዱ የቀረበውን ቅሬታ ተቀብለው፣ የተሠራ ነገር ቢኖርም ትልቅ ዳገት እንደሚጠብቅ ገልጸዋል፡፡ የአመራር አባላት ራሳቸውን ማጥራትና ወደ ራሳቸው መመልከት እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል፡፡

ዶ/ር አርከበ በጉባዔው ንቁ ተሳትፎ ያደረጉ ሲሆን፣ ሕዝቡ ቅሬታ እያቀረበ ያለው በፍትሕ አካላትና በፓርቲው አባላት መሆኑ አሳሳቢ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ጉባዔው ዛሬ የሚጠናቀቅ ሲሆን፣ የሥራ አስፈጻሚና የማዕከላዊ ኮሚቴ እንዲሁም የቁጥጥር ኮሚሽን አባላትን ይመርጣል፡፡

11ኛው የብአዴን ድርጅታዊ ጉባዔ በባህር ዳር በድርጅቱ ሪፖርት ላይ ተወያይቷል፡፡ ጉባዔው በክልሉ የተመዘገበውን የኢኮኖሚና ዕድገትና የግብር ምርት ውጤታማነት የገመገመ ሲሆን፣ ኢኮኖሚያዊ ዕድገቱ 10.4 በመቶ በመድረሱ የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ መቻሉ ተገልጿል፡፡ የመጀመርያው የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ፣ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች፣ መልካም አስተዳደር፣ ትምህርት፣ ጤናና ሌሎች መስኮችም በግምገማው ተካተዋል፡፡

መልካም አስተዳደርን በተመለከተና በሥራ ፈጠራ ጉድለቶች መኖራቸውን የገመገመው ጉባዔው፣ የክልል ከፍተኛ አመራሮችም ለችግሩ ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዙ አውስቷል፡፡ የድርጅቱ ጉባዔ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት፣ የብአዴንና የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን፣ የድርጅቱን ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር በመምረጥ ማክሰኞ ምሽት ተጠናቋል፡፡ ማክሰኞ ምሽት የተመረጡት እነማን እንደሆኑ ግን አልታወቀም ነበር፡፡

ኢሕዴድ በአዳማ ከተማ 8ኛ ጉባዔው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል፡፡ በጉባዔው በክልሉ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን ለማምጣት የሚችሉ አዳዲስ ሐሳቦች እንደ ግብዓት ሲሰባሰቡ እንደነበር ተገልጿል፡፡ በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን በክልሉ የ11.2 በመቶ ዕድገት ለማስመዝገብና የኢኮኖሚውን መዋቅራዊ ሽግግር ለማፋጠን የሚያስችሉ ውሳኔዎች ይተላለፋሉ ተብሏል፡፡

የኦሕዴድን ድርጅታዊ ህልውና ይፈታተናሉ የተባሉት ትምክህትና ጠባብነት፣ ኪራይ ሰብሳቢነት፣ የተንዛዙ አሠራሮችና ፍትሐዊነት የጎደላቸው አመራሮች በጉባዔው ወቅት መነሳታቸው ታውቋል፡፡ ላለፉት ሦስት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የኦሕዴድ ጉባዔ ማክሰኞ ምሽት ማተሚያ ቤት እስከገባንበት ጊዜ ድረስ ይጠናቀቃል ተብሎ እየተጠበቀ ነበር፡፡

የደኢሕዴን ጉባዔ በሐዋሳ ማክሰኞ ነሐሴ 19 ቀን 2007 ዓ.ም. ተጠናቋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ሊቀመንበር ሆነው እንዲቀጥሉ ሲመረጡ፣ የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ለምክትል ሊቀመንበርነት ተመርጠዋል፡፡ ጉባው በሦስተኛ ቀን ውሎው የመጀመርያውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ገምግሞ፣ በምግብ እህል ራስን መቻል ላይ አበረታች ውጤት መገኘቱን ተወያይቶበታል፡፡

አበረታች የተባሉ ስኬቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ፣ ይቀራቸዋል የተባሉት ላይ ደግሞ በተጠናከረ ሁኔታ ርብርብ እንዲረደረግ ውሳኔ ተላልፏል፡፡ የጤናና የትምህርት ዘርፍ ተደራሽነታቸው መልካም መሆኑ ተወስቶ፣ የጥራት ጉዳይ ግን እንዲታሰብበት ማሳሰቢያ ተሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም ጠባብነት፣ ብልሹ አሠራርና ሙስና በድርጅቱ ውስጥ ቦታ እንደማይኖራቸው ውሳኔ ላይ መደረሱ በውይይቱ ወቅት ተነስቷል፡፡ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት፣ የደኢሕዴንና የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ አባላትም ተመርጠዋል፡፡ የተሟላ ዝርዝር ግን ማግኘት አልተቻለም፡፡

በተያያዘ ዜና የብአዴን ነባር ታጋይና ከፍተኛ አመራር የነበሩት አቶ አዲሱ ለገሠ በክብር መሰናበታቸው የተገለጸ ሲሆን፣ አቶ ዮሴፍ ረታም እንዲሁ ተሰናብተዋል፡፡ የደኢሕአዴን ሊቀመንበር፣ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል በመሆን ያገለገሉት ዶ/ር ካሱ ኢላላ እንዲሁ ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት በክብር መሰናበታቸው ተገልጿል፡፡   Source ( Reporter )

Friday, August 21, 2015

ፍርድ ቤቱ ሃብታሙ ኣያሌውን ጨምሮ ኣምስት ተከሳሾችን በነጻ ኣሰናበተ ::
መከላለክል  ሳይጠበቅባቸው በነጻ እንዲሰናበቱ የተወሰነላቸው ዳንኤል ሺበሺ፣ አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ሃብታሙ አያሌው እና አብርሃም ሰለሞን ናቸው::
የፌደራሉ አቃቤ ህግ በብይኑ ቅር በመሰኘቱ ይግባኝ እጠይቃለሁ ብሏል።የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19 የወንጀል ችሎት በሽብር ወንጀል ከተከሰሱ የቀድሞው የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌውን ጨምሮ 10 ግለሰቦች መካከል አምስቱን በነፃ ሲያሰናብት ቀሪዎቹ እንዲከላከሉ ብይን ሰጠ።
የፌደራሉ አቃቤ ህግ በብይኑ ቅር በመሰኘቱ ይግባኝ እጠይቃለሁ ብሏል።
የሀገሪቱን መሰረታዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ህገ መንግስታዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ወይም ማህበራዊ ተቋማትን ለማናጋት እና ለማፈራረስ በሚንቅሳቀው ራሱን ግንቦት 7 እያለ በሚጠራው የሽብርተኛ ድርጅት ውስጥ አባል ለመሆን እና የሽብር ድርጅቱ የሚሰጠውን ማንኛውም አይነት ተልዕኮ ለመወጣት ተንቀሳቅሰዋል በሚል ክስ የተመሰረተባቸው ግለሰቦች፥ ዘላለም ወርቅአገኘሁ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሺ፣ አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ዮናታን ወልዴ፣ አብርሃም ሰለሞን፣ ሰለሞን ግርማ፣ ባህሩ ደጉና እናተስፋዬ ተፈሪ ናቸው።
የፌደራል አቃቤ ህግ ግለሰቦቹ 2000 . ጀምሮ ከሽብር ድርጅቱ ጋር ግንኙነት በመፍጠር በተለያዩ ማህበራዊ ድረ ገፆች መረጃ በመለዋወጥ ኢትዮጵያ ውስጥ በአረቡ አለም የተከሰተውን አመፅ ለመተግበር የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን አድርገዋል እና ከሽብር ድርጅቱ የሚላክላቸውን ገንዝብ እስከመቀበል ደርሰዋል የሚለውን በማተት በጥቅሉ አራት የሽብር ወንጀል ክሶችን ነው የመሰረተባቸው።
አቃቤ ህግ ክሱን ያስረዱልኛል ያላቸውን የሰው ምስክርና የሰነድ ማስረጃዎችን አሰምቷል።
ምስክሮቹ እንደ ክስ አስረድተዋል ወይም አላስረዱም የሚለውን መርምሮ ለብይን በያዘው ቀጠሮ መሰረት ዛሬ ችሎቱ አቃቤ ህግ ከተከሳሾቹ መካከል ዳንኤል ሺበሺ፣ አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ሃብታሙ አያሌው እና አብርሃም ሰለሞንን መከላከል ሳይጠበቅባቸው በነፃ ይሰናበቱ ሲል በይኗል።
ሌሎች አምስቱ ተከሳሾች ይከላከሉ ብሏል።
ይሁን እንጂ በነጻ ይሰናበቱ ከተባሉት መካከል ዳንኤል ሺበሺ እና የሺዋስ አሰፋ መጋቢት 1 2007 . ችሎት በመድፈር ወንጀል 1 አመት 2 ወር እንዲሁም አብርሃ ደስታ ደግሞ 1 አመት 4 ወር እስራት የተቀጡ በመሆኑ እስራታቸውን ሲጨርሱ ነው የሚለቀቁት።
ሃብታሙ አያሌውና አብርሃም ሰለሞን የቀደመ ቅጣት ስለሌለባቸው ዛሬውኑ የእስር መፍቻ ተፅፎ ይለቀቁ ብሏል ችሎቱ።
ችሎቱ በኢግዚቢት የተያዘ የተከሳሾች ንብረት ካለ ይመለስላቸው ሲልም ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ችሎቱ በሌሎች የተጠቀሰውን አንቀፅ ሳይቀይር ዘላለም ወርቅአገኘሁ የሽብር ወንጀሉን በማነሳሳት፣ በማሴርና በማቀድ የተጠቀሰውን የፀረ ሽብር አንቀፅ አራትን የሽብር ወንጀል ውስጥ በመሳተፍ በሚለው ተቀይሮ ይከላከል ብሏል።
ይከላከሉ በተባሉ ተከሳሾች ላይ ፍርድ ቤቱ የመከላከያ ምስክር ለመስማት ለህዳር 13 ቀን 2008 . ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።
ምንጭ፡ አዲስ አበባ ነሃሴ 14 2007 (ኤፍ..)

60 በመቶ የሶማሊያ ክፍል ከአልሸባብ ነፃ መሆኑ ተገለጸ።

ይሁን  እንጂ  ኢትዮጵያ አልሸባብን የማዳከም ስራ እየሰራች ቢሆንም በሶስቱ ቀጣናዎች ገና የማጥቃት እንቅስቃሴ ባለመጀመሩ አልሸባብን ሙሉ በሙሉ ከሶማሊያ ለመደምሰስ አለመቻሉንም በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ወንድሙ አሳምነው ተናግረዋል።

በአሚሶም ስር የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ የሶማሊያ ጦር እና ከአሚሶም ውጪ የተሰማራው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በጥምረት በከፈቱት የተጠናከረ ዘመቻ 60 በመቶ የሶማሊያ ክፍል ከአልሸባብ ነፃ መሆኑ ተገለጸ።
በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ወንድሙ አሳምነው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፥ በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ (አሚሶም) ስምሪት በአራት ቀጣና የተከፋፈለ ነው።
በቀጣና አንድ ኡጋንዳ፣ በቀጣና ሁለት ብሩንዲ፣ በቀጣና ሦስት ኢትዮጵያ እንዲሁም በቀጣና አራት ኬንያ ተልዕኮ ተሰጥቷቸዋል።
የሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት ለእኛ ትርጉም አለው ያሉት አምባሳደሩ፥ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል ከሶማሊያ ሠራዊት ጋር በጥምረት በከፈቱት ጥቃት አልሸባብን ማዳከም መቻላቸውን ተናግረዋል።
ከአልሸባብ ነጻ የወጣው 60 በመቶ የሶማሊያ ክፍል ከኢትዮጵያ ጋር የሚዋሰን በመሆኑ ለሰላሟ ትልቅ ጥቅም አለውም ብለዋል።
ኢትዮጵያ የሶማሊያ መንግሥት ሠራዊት እንዲጠናከርና ነፃ በሆኑ አካባቢዎች አስተዳደር እንዲመሰረት ለሶማሊያ መንግሥትና ህዝብ ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥልም ነው ያስረዱት።
በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በአሚሶም ጥላ ስር አልሸባብን ለማዳከምና ለማክሰም ከኢጋድ አባል አገሮች ጋር በትብብር እየሰራች መሆኑን ገልፀው፤ ወደፊትም በአካባቢው ሰላምና ልማትን ለማምጣት ይበልጥ ትብብሯን ታጠናክራለች ብለዋል።
Source: - (ኤፍ. . )

Sunday, August 16, 2015

ኣቶ ሬድዋን ሁሴን ከዲያስፖራ የሶሻል ሚዲያ ኣባላት ጋር ውይይት ኣደረጉ::


በሚዲያ ስራ ላይ የተሰማሩ የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ከመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች /ቤት ሚኒስትር ከክቡር አቶ ረድዋን ሁሴን በሀገረ ገጽታ ግንባታ ዙሪያ የጋራ ውይይት አደረጉ::

የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች /ቤት ሚኒስትር ክቡር አቶ ረድዋን ሁሴን በሚዲያ ስራ ላይ የተሰማሩ የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በጽቤታቸው ተቀብለው ባደረጉት ውይይት መንግስት እያከናወነ ያለው የልማትና የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ስራዎች በተሰራው ልክ በቂ የሚዲያና የኮሙዩኒኬሽን ስራ ሽፋን አግኝቷል ማለት አይቻልም። ይህንን ችግር ለመፍታት በመንግስት በኩል የኮሙዩኒኬሽንና ሚዲያ ባለሙያውን አቅም በማሳደግ ለህብረተሰቡ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል ስራ እየተሰራ ሲሆን በተለይ በኮሙዩኒኬሽን ዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎች በየተቋማቸ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች በተለያዩ ሚዲያዎች ለህብረተሰቡ መረጃ ተደራሽ እንዲያደርጉ የሚያስችል መመሪያ በማውረድ በየተቋሙ ተግባራዊ እንዲሆን ጥረት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል


እንዲሁም መንግስት የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ፖሊሲዎችን አውጥቶ ከባለድርሻ አካለት ጋር ውይይት እያደረገ ሲሆን ፖሊሲው በሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶች ባለሙያዎች በጋራ የሚያሰራና የሀገሪቱን ገጽታ ግንባታ ስራ በተናበበና በተቀናጀ ሁኔታ ለመምራት የሚያስችል ነው ብለዋል።
የዲያስፖራ ማህበረሰቡም ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የሚያስችል የጋራ የሆነ አሰራር ስለሌለን በሀገሪቱ እየተከናወኑ ያሉ የልማትና የዲሞክራሲ ስራዎች በአግባቡ ለውጭው ማህበረሰብ እያደረስን አየደለም ሰለሆነም ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ የምናገኝበት አሰራር እንዲዘረጋልን እንፈልጋለን ብለዋል።
ክቡር ሚኒስትሩም እንዳሉት የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ፖሊሲው ውይይቱ አልቆ ሲጸድቅ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭው የሚገኙ ሚዲያዎች ወጥ የሆነ የመረጃ ቅብብሎሽ ስርዓት እንዲኖር የሚያስችል አሰራር እንዘረጋለን እንዲሁም ወቅታዊ መረጃዎችን በጽ/ቤቱ ዌብ ፖርታል እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያ እንዲደርሳችሁ የምናደርግ ሲሆን በተለይ አጫጭር ዶክመንተሪዎች 5-7 ደቂቃ የሚሆኑ ደክመንትሪዎች ለሚዲያ ግብዓት በሚሆን መንገድ ለመስራት የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን በወቅቱ እንዲደርሳቹ ይደረጋል። የሚያጋጥማችሁን ችግሮች በጋራ ተቀራርበን በመስራት የምንፈታቸው ሲሆን ለኢትዮጵያውያንም እና ለውጭው ማህበረሰብ በሀገራችን እየተከናወኑ ያሉ የልማትና የዲሞክራሲ ስራዎች የማስተዋወቅ ስራ በጋራ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።  Source (Government Communication Affairs Office).