Wednesday, July 29, 2015

የግንቦት ሰባቱ ቁልፍ ሰው መጽሃፍ በመጻፍ ላይ ናቸው::
እንደ ኢትዮጵያው  የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴዎዶርስ  ኣድሃኖም ገለጻ የግንቦት ሰባት ዋና ሰው ኣቶ ኣንዳርጋቸው ጽጌ  በመንግስት ፍቃድ ላፕ ቶፕና ሌሎች  የሚፈልጉት ቁሳቁሶች ገብተውላቸው መጽሃፍ በመጻፍ ላይ በመሆናቸውና እንደውም ወደ ማገባደዱ ደርስዋል::  ኣንድ ከፍተኛ የመንግስት ባለ  ስልጣን እስረኛውን  ኣቶ  ኣንዳርጋቸውን በተመለከተ መግለጫ ሲሰጥ  ዶክተር ቴዎድሮስ የመጀመሪያው ናቸው ::
ዶክተር ቴዎድሮስ ኣቶ ኣንዳርጋቸው በመኪና ተደርገው በቻይና መንግስት ትብብር የተሰራውን  ያዳማ ናዝሬትን መንገድ እንደጎበኙና በዚህም እንደተደነቁ ይፋ ኣድርገዋል::  ወደፊትም የተለያዩ ቦታዎችን ሊጎበኙ  እንደሚችሉና በጥሩ  ኣያያዝም ላይ እንዳሉ ሳይጠቅሱ ኣላለፉም::
  ዶክተሩ ኣቶ ኣንዳርጋቸው መጽሃፍ በመጻፍ ላይ ናቸው ቢሉም ስለ መጽሃፉ ይዝትና በምን  ጉዳይ ላይ እንደሚጽፉ ከመግለጥ ተቆጥበዋል  የፍርድ  ሂደታቸውንም  በተመለከተ ሲያስረዱ "ይሄ የህግ ጉዳይ ነው ህጉ ኣቶ ኣንዳርጋቸውንን በሁለት ጥፋት ከሶ በሌሉበት ውሳኔ  ኣስተላፎባቸዋል ህን ውሳኔ ተገኝተው ይግባኝ ባለማለታቸውና ባለመከላከላቸው በተገኙበት በሰላማዊ መንገድ ሆነ በሃይል ከተያዙ መጀመሪያ የተወሰነባቸው ህግ እንደሚጸና ህጉ ያዛልብለዋል::  

0 comments:

Post a Comment