Sunday, April 26, 2015

ኣይሲስ የሱኒ ጠባቂ?? ወይስ የራሱን መንግስት ኣጥባቂ??እምናን እንዴት ኣደራችሁ ? እንዴት ሰነበታችሁ?    ኣሰላማሌኩም ኢትዮጵያዊ ሙሲሊም ወንድሞቼ እህቶቼ..

ኣንዳንድ የተሰማኝን ወይም የደረስኩበትን ነገር እስኪ ጫር ጫር ላደርግላችሁ.. ዜናውን ያገኘሁት ድሬ ቱዩብ ላይ ወጥቶ ነው ጉዳዩ ስለ የመን ወቅታዊ ሁኔታ ቢሆንም የሚገልጸውየጎረቤት ጉዳይ ነገ ያንተ ጉዳይም ይሆናልበሚል ህሳቤ እንደ አለታዊ ዜና ላልፈው ኣልፈለኩም በሊቢያ በወገኖቻችን ላይ በደረሰው ሰቅጣጭ ዜና ፤እንዲሁም የደቡብ ኣፍሪካው የጥቁር ዘረኝነት የሁላችንንም ቀልብ ይዞ ስለነበር ስለ የመን ወቅታዊ ሁኔታ ቡዙዎቻችን ወቅታዊ መረጃ  (update)  ያለን ኣልመሰለኝም የመን በሻይትና በሱኒ እምነት ተከታዮች መካከል ሳንድዊች እየሆነች ነውበዚህ ሳንድዊች ውስጥ የኛው ወገኖች እንዳሉበት ኣይረሳ፦፦ ሱኒዎችን ሳውዲ ኣረቢያ በግልጽ ስትደግፍ ንደውም ባየር በመግባት ተደጋጋሚ ጥቃት ስታደርስ ሻይቶችን ደግሞ ኢራን እንደምትደግፍ መረጃዎች ይገልጻሉ::  እንደውም ኢራኖች በጥንቃቄ እቃ የጫነ መርከብ የሚመስል ወደ የመን እያስጠጉ ሲሆን ውስጥ ውስጡን የሚነገረው ለሻይት እምነት ተከታይ የመኖች የሚሰጥ የጦር መሳሪያና የህክምና ቁሳቁሶች እንደሆኑ ይነገራልሃሜት ነው መርከቡን ኣስቁሞ የፈተ ወይም ለመፈተ የደፈረ እስካሁን ማንም የለም:: ሱኒዎች ያካባቢው መንግስታት ድጋፍ ኣላቸው.. እንደውም ግብጽን ,ኮታርን , በዋናነት ደግሞ ሳውዲ ኣረቢያን የያዘ የሚሊተሪም ሆነ የሎጂስቲክ ድጋፍ ያገኛሉ:: ይሀን ያህል ካልኩ በኌላ ግን ሳውዲ ኣረቢያሚሽ ኔን ጨርሻለሁ” (Mission accomplished)  ባለች ሰኣታት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የሻይት ተዋጊዎች ዋናውን የሱኒ የመናውያንን የጦር እከል ወይም Command Center  በጃቸው ኣስገቡት:: ይሄ የሚያሳየው ሽያቶቹ ተዋጊዎች በምድር ውጊያ ሃይለኛ ስለ መሆናቸው ማስረጃ ነው:: ኢራንንም እኮ ብትሆን በምድር ለምድር ውጊያ ኣትታማም!! የኬሚካል ጦር እየዘነበባቸው የኢራቅን ሱኒ ጦር ምሽ ጋቸው ድረስ እየገቡ ያንቁ እንደነበር ታሪካቸው ይናገራል :: ይሄ እንዳለ ሆኖ ግን ወገኖቻችን ሌሎችንም ክርስቲያኖች በሶርያ በግብጽ እንዲሁም በኢራቅ እያረደና መስቀል ያለበትን ስፍራ ሁሉ እያፈረሰና እያወደመ ያለው ያይሲስ ወታደራዊ ክንፍ ኣሁን ወድ የመን እየሄደ መሆኑን ክድህረ ገጻቸው ላይ ከወጣው ቪዲዮ ላይ ማየት ችያለሁ ( ዜናው ድሬ ትዩብ ላይ ኣለ) :: መልክታቸው ደሞ ኣስገረመኝ “.... ደም የጠማው የኣይሲስ ወታደር የሻይቶችን ጉሮሮ ለመቁረጥ በመምጣት ላይ ይገኛል …” ይላል ከዛም በመቀጠል “.. የመንን ለሱኒዎች እናስመልሳለን..” ሲል ይገልጻል::
“የመን በታሪክም የሱኒዎች እንጂ የሺያቶች ኣትሆንም!! መጥተን እንጭርሳች ሁኣለን..”  የሚል የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ክፍተዋል:: ኣስተውሉ ይሄ የሆነው ሳውዲ ኣረቢያ ያየር ጥቃቱን ኣቁሜኣለሁ የሽያቶችን ኣከርካሪ ሰባሬኣላሁ ካለች በሗላና ሽያቶቹ የሱኒን ኮማንድ ሴንተር በጃቸው ማስገባታቸው ከተረጋገጠ በሗላ ነው::
ሳውዲ ኣረቢያ ኣይሲስን በገልጽ እደግፈዋለሁ ብላ በሙሉ ልብ ባትናገርም ሽያቶችን, ሂዝቦላዎችን, ታሊባኖችን ..ኣይሲስ በጠላት ኣይን ስለፈረጃቸው የሞራል ድጋፍ እንደምት ሰጠው ምንም ኣያጠራጥርም ምናልባትም እኮ ወገኖቻችን የሚታረዱበት ቢላና ጭንቅላታቸው የሚበረቀስበት ኤኬ 47 ጠመንጃ ከዶላር ጋር የምታሽ ራቸው ሳውዲ ላለመሆኗ ምን ማስረጃ ኣለን???
ሳውዲ ኣረቢያ በትልቁ የወሃቢዝም እምነት ወይም ኣመለካከት ተከታይ ደጋፊና ዋናዋ ኣቀንቃኝ ናት:: ይሄ የወሃቢዝም ዶክትሪን ኣይሲሶዎችንከበረሃ የመጡ ኣዳኞቹ ኣድርጎ ያያቸዋል ?? ወይስ ጸረ ኢሲላም ናችሁ ብሎ ይፈርጃቸዋል??ያለ ማጋነን  ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ   ወቅታዊ ጥያቄ ይመስለኛል  እስኪ ሳትቸኩሉና ስሜታዊ ሳት ( ሳንሆን ) ይሄን ነገር በጽሞና እንወያይበት!! “ውጊያ ከመግባት በፊት መጀመሪያ ጠላትህንና ወዳጅህን ለይ… በፍሬንዲሊ ኣታክ (friendly attack) የራስህንም ሰዎች እንዳትጨር !!” ይላል ማን ኣለ ? ብትሉኝ መልሴ እኔም ኣላውቀውም ነው….ብቻ ውስጤ የነገረኝን ነው የጫጫርኩላችሁ ..!!
Have your say…
 For daily Ethiopian news and events, please click our site at http://www.ethiopianthisweek.com and http://www.ethioonutube.com.
Have questions or suggestions? Please send us your comment to ethiopianthisweek@gmail.com.
You can also listen our weekly radio show by dialing 712-432-9790 it is absolutely free and no access code required
Thanks,
ETW Editor

0 comments:

Post a Comment