Thursday, April 23, 2015

ዋናው ጉዳይ!!የተከበራቹ ጦማርያንና ጦማርያት አንዲሁም ኣንባቢያንና  ኣንባብቢያት መረጃ ስንሰጥ ምርኩዛችንና ኣለቃችን  ህሊናችን መሆን  ይገባዋል እውነተኛ ሰው ኣለቃው ህሊናው ነው ባካባቢው የሚሰማው  ጫጫታና ሁካታ መሆን ኣይገባውም በሊቢያ ሆነ በደቡብ  ኣፍሪካ በተፈጠረውና ምናልባትም ገና ሊፈጠር በሚችለው ኣሰቃቂ ድርጊት ከሁሉም ወገን ፖሎቲካዊ ትርፍ ለማግኘት መጣደፍ ኣገር ወዳድ ኣያሰኝም በዚህ ሰኣት ሁላችንም  መንግስትም ሆነ የተቃዋሚ ፖሎቲካ ድርጅቶች እጅ እጅ የምንያያዝበትና ኣብረን በጋራ ቆመን ( ኣክንባሎና ምጣድ በመሆን ) ኣይሲስና የስሜት ኣጋሮቹን እንደ ድፎ ዳቦ ከላይና ከታች የምንለበልብት ሰኣት ነው ::  በፖሎቲካዊ ኣስተሳሰባችንና ኣቌማችን ተለያይተን የቆምንባቸው ሰኣቶችና ጊዜያቶች ያሉትን ያህል ኣብረን በጋራ ቆመን ኣገራዊ ዜማ የምናሰማበት ወቅቶች ሊኖሩን ይገባል::  ሪፐብሊካንስና ዲሞክራት ምነታቸው ፖሎቲካዊ ኣስተሳሰባቸው ሳቢያ ያይጥና የድመት ያህል የሚናቆሩበት ጊዜ ጥቂት ኣይደለም… ካፈጣጠራቸው እንኴን ስናይ  ኣንዳቸው ኮንዘርቫቲቭ ሲሆኑ ሌላቸው ደግሞ የሊበራል እምነት ኣራማጆች ናቸው::
 ይሁን አንጂ ባገራቸው የጋራ ጥቅም ኣንጻር ኣብረው መቆምም ይችሉበታል!!  ወገኖቻችንን  ያይሲስ ቅጥረኞች በጠራራ ጸሃይ ላህ ዋክበርእያሉ እንደ በግ እያረዱ ከዚህ የፖሎቲካ ትርፍ ለማምጣት እርስ በርሳችን እንሽቃደማለን::  መጀመሪያ ኣገራችንንና ህዝባችን ከመሰሪዎች ዘብ ሆነን እንጠብቅ::
 በጋሪሳ ዩኒቨርስቲ የተፈጸመው ወይም በኬንያ ሞል ውስጥ የተፈጸሙት ኣሰቃቂ ድርጊቶች ባገራችን ላይፈጸሙ የማይችሉበት  ምንም ምክንያት የለም::  ኢትዮጵያ ሁሌ እንደተዛተባት ነው ለኛ የተለየ መልኣክ  ኣይመጣም::  ያገራችን  የደህንነት ሃይሎች እስካሁን ድረስ ኣጥር ሆነውልናል::  ኣልሽባብም ሆነ ኣልታይድ እንዲሁም ስማቸውን የማልጠቅሳቸው ያይሲስ የስሜት ደጋፊውች በኬንያ ወይም በዩጋንዳ የፈጸሙትን ያልፈጸሙት ያገራችን የመከላከያ ሃይልና የደህነት ሃይሎች 24  ሰኣት ተግተው በመጠበቃቸው ነው::  እንደውም ከጂኦግራፊ ኣቀማጠጣችንና ከስብጥራችን ኣንጻር ለጥቃት  የምንመቸው እኛ ነን ይሄ የፖሎቲካ ትርፍን የማግኘት   ጥያቄ ኣይደለም… ይልቁንም ያገርንና የህዝብን ህልውና የማዳን ጥያቄ ነው::   ቅኝታችንን ባግባቡ እንቃኘው!!  በኔ እምነት መንግስት ህጋዊ ለሆኑት ኣገራዊ የፖሎቲካ ተቃዋሚዎች ይህ የጋራ ችግራችን ስለሆነ ኣብረን በጋራ እንስራ በጋራ እንቁም የሚል ጥሪ ማቅረብ ኣለበት ብዬ ኣምናለሁ ይሄን ሃላፊነት እነሱም መሽከም ኣላባቸው::  ተቃዋሚዎችም ጊዜያዊ የህዝብን ስሜት ለመግዛት ቆጠብ ብለው ለችግሩ   ዘለቄታዊና ኣገራዊ መፍት ላይ ማነጣጠር ኣለባቸው  ብዬ ኣምናለሁ::
 ሰው እንደ በግ አየታረደ ፖሎቲካውን ለጉልት ሽመታ ኣናቅርበው!!  ኣንዳንዴም ባንድ ቌንቌ  መነጋገርን እንልመድ..!  ብስለትና ስክነት ይሉሃል ይሄ ነው:: last but not the least  የናይጄሪያውን መሪ ሙሃምድ ቡሃሪ ለስልጣን ያበቃቸው ካለውና ኮራፕትድ ከሆነው የጉድ ላክ ጆናታን መንግስት በተሻለ ቦኮ ሃራምን ኣፈር ከድሜ ኣስግጠዋለሁ ስላሉና ለዛ የሆነ  ስትራተጂ ለህዝቡ ስላቀረቡ እንጂ ክፍተቱን ለፖሎቲካ ትርፍ  በመጠቀም ኣይደለም::

For daily Ethiopian news and events, please click our site at http://www.ethiopianthisweek.com and http://www.ethioonutube.com. 
Have questions or suggestions? Please send us your comment to ethiopianthisweek@gmail.com
You  can also listen our  weekly  radio show  by dialing 712-432-9790  it is absolutely  free and no access  code  required

Thanks,
ETW Editor

0 comments:

Post a Comment