Sunday, April 19, 2015

የደቡብ ኣፍሪካው ጉዳይ የግል ኣስተያየት::
ሰሞኑን  በደቡብ ኣፍሪካ በወገኖቻችን ላይና በሌሎች ኣፍሪካውያን ወንድሞቻችንና   አህቶቻችን ላይ የተፈጸመው ግፍ ሁላችንንም ኣስቆጭቶናል..  ኣሳዝኖናል…!!  ደቡብ ኣፍሪካ ካፓርታይድ ነጻ  አንድትወጣ በግንባር ቀደምትነት ኣገራችን እንዲሁም ሌሎች ያፍሪካ ኣገሮች ቡዙ መስ ዋአትነትን ከፍለዋል::  ኣገራችን ኢትዮጵያ ለማንዴላ በኢትዮጵያ ፓስፖርት አንዲንቀሳቀስ ከማድረጔም በላይ ኤን ( ANC ) የህቡእ  እንቅስቃሴ  አንዲያደርግ  ኣስፈላጊውን ኣድርጋለች ሌሎችም ያፍሪካ ኣገሮች ለደቡቡ  ኣፍሪካ ነጻ መውጣት የሚቻላቸውን ኣድርገዋል  ጊዜ ኣለፈና  ዙሉዎቹ ወንድሞቻችን ይሄን ረሱት::   ኣንዱ የነብር ቆዳ መልበስ የሚወድ  የዙሉ ንጉስየውጭ ዜጎች ይውጡ!”  የሚል ዘረኛ ጥሪ ለተከታዮቹ  ኣስተላለፈየሆነውን ሁላችንም አያየን ስለሆነ መድገም ኣያስፈልግም::
 የሰማይ ኣምላክ  በኣሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው ላለፈው በሙሉ እረፍትና ሰላም ባለበት በነገት ያሳርፍልን  ንብረታቸው ለተዘረፉና ለተጎዱትም መጽናናትን ይስጥልን::  
  ይህን ካልኩ በሗላ ግን የታዘብኩትን ላካፍላቹ ኣንዳንድ ያፍሪካ ኣገር ወንድሞቻችን ባገራቸው ያሉትን ያገኙትን ደቡብ ኣፍሪካውያን ሲያገኙ እንደ ማርያም ጠላት መቀጥቀጥ  ጀመረዋል  ኣንዳንዶቻችንም ቁጭታችንን ያበረደልን ስለሚመስለን ይሀን ቪዲዮ እየተቀባበልን አናሳያለን እነዚህ በሌላ ኣገር የሚኖሩ ሰላማዊ ደቡብ ኣፍሪካውያን ደርባንና ኣካባቢዋ ለተፈጸሙ ወይም ለሚፈጸሙ ግፎች ተጠያቂ ናቸው ብዬ ኣላምንም::  ቀጥታ ተጠያቂዎቹ  በዋናነት የዙሉ ጎሳ መሪ ሲሆን በተከታይነት  የደርባን ቦዘኔዎች ናቸው አነዚህ ኢትዮጵያዊውም ሆነ ሌላው ሰርቶ ጥሮና ደክሞ ባገኘው ንብረት  ራሱንና ቤተሰቡን ሲለውጥ በማየታቸው በቅናት  ኣይናቸው ደም የለበሰና ለመዝረፍና ንብረታቸውን ለማውደም አቺ  ኣጋጣሚ ከሰማይ እንድትወርድ  ይጠብቁ የነበሩ የሳጥናኤል ልጆች ናቸው::
  የደቡብ  ኣፍሪካ መንግስት አንዲሁም  የጸጥታው ሃይል ወገኖቻችንን  የሚታደግ ሰላም ኣስከባሪ  ባካባቢው ማሰማራትና ኣጥፊዎችንም ለፍርድ ማቅርብ  አንዲሁም በዚህ ኣሰቃቂ ድርጊት ህይወታቸው ለጠፋ ካሳ መክፈል ይጠበቅበታል::  አኛም በመተባበር በደቡብ ኣፍሪካ መንግስት ላይ ጫና ማድረግ ይጠበቅብናል::   በያገሩ የሚኖሩትን ሰላማዊ ደቡብ ኣፍሪካውያንን መደብደብና ማዋረድ ካገር አንዲወጡ ማድረግ ተጨማሪ ዙሉዎችን  መፍጠር ነው::  አኛም የነሱ ደቀ መዝሙር አየሆንን ነው!!  ሟርተኛ ኣትበሉኝ እንጂ የሁቱና የቱሲ እልቂት ሲጀመር አንደዚህ ነበር ::
ሌላው ያስተዋልኩት ነገር ኣንዳንድ ያገራችን ዘፋኞች ማስታወቂያ መስል  የሃዘን መግለጫ ኣይሉት ወይምእኔስ ከማን ኣንሼ  ኣይነት መል አክት በተለያዩ የፌስ ቡክ  ገጾች ላይ  በግልም በጋራም ሆነው ሲያሰሙ ኣይቻቸዋለሁ::  ሃዘንተኛ ለመምስልም ኣይናቸውን ሰፌድ በሚያክል መነጽር ጋርደውታል::  ይቺ የነጭ ፈረንጆች ብልጠት ናት::  ነጾች በቀብር ጊዜ  ሲያለቅሱ አንዳይታይባቸው ወይም ኣለማልቀሳቸው እንዳይጋለጥባቸው ጥቁር መነጸር ኣይናቸው ላይ ይገደግዳሉ የኛዎቹም ወገኞች ይቺን ተምረዋል::  
 ኣንዱ ኣቅራሪ እንደውም ምናለ በሱ ቤትን ማጽናናቱ ነው አንግዲ ..” ኣምላክ የሰራነው ግፍ በቃን አንዲለንና  ፊታችንን አንዲመልስልን       እንግባ..!! ”  ኣለውና ኣረፈው::  ስው  ለፍቶ ወጥቶ ጥሮና ደክሞ ያገኘውን ንብረትና ሃብት ገጀራ በያዙ ማጅራት መቺዎች ሲዘረፍ ይሄ ወገኛ ኣዝማሪ ግፍ ስላለብህ ነው ይለናል… ጉድ አኮ ነው::
  ይልቁኑ ኣዝማሪዎች ሆይ እንዲሁም ስፓንሰሮች ኣንድ ነገር በዚህ ወቅት ድረግ ያለባቹ ይመስለኛል  ለወገን ደራሽ ወገን ነውበሚል በደንብ ኮኦርድኔት ( coordinated )  የተደረገ ኮንሰርት ኣዘጋጁና ኢትዮጵያውንም ሌላውንም ዜጋ ጋብዛቹ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በማዘጋጀት የተጎ ወገኖቻችን የሚረዱበትን መላ ከመላው ኣገር ወዳድ  ኢትዮጵያዊ ጋር በመሆንና በመቀናጀት ኣብረን በጋራ ጥረት አንጀምር!!  ያንድ ደቂቃ የሃዘን መገለጫ ክሊፕ ማስተላለፍ ማስታወቂያ ለመስራት እንጂ መፍት ኣይደለም:: 
የሰማነውን በልቦናችን ያውልልን:: ኣሜን! ኣሚን! ሀሌሉያ!! 
For daily Ethiopian and its vicinity news, click our site at http://www.ethiopianthisweek.com or http://www.ethioonutube.com. You may also listen our weekly radio show by dialing 712-432-9790.  It is free and no access code required.

0 comments:

Post a Comment