December 7, 2014 Ethiopian This Week Radio Program
ዶ/ር አበራ በኮምፕዩተር
ግዕዝ ፊደልን ለመጀመሪያ ጊዜ መጠቀም እንዲቻል ያደረጉ ምሑር ናቸው። ይሀንንም ያደረጉት የዓማርኛውን የጽሕፈት መሣሪያ (ታይፕራይተር) ለሚያውቁት ቀላል እንዲሆን በ“a”፣ “b”፣ “c”፣ “d” ምትክ “ሀ”፣ “ጠ”፣ “ሸ”፣ “ዘ” እና እንግሊዝኛ
ለሚያውቁ በ“A”፣ “B”፣ “C”፣ “D” ምትክ “አ”፣ “በ”፣ “ቸ”፣ “ደ” ቀለሞችን በመመደብ ዓይነት ሰላሳ ሰባቱን የግዕዝ ቤት ሆህያት ለ፴፯ የኮምፕዩተር መርገጫዎች ስሞችም በማድረግ ነበር። ስምንቱን የፊደል ቤቶች ወይም እንዚራን ስምንት ፎንቶች ላይ በተኑዋቸው። በእዚህ ዘዴ በእጅ ጽሑፍና ማተሚያ ቤቶች ብቻ ይታተሙ የነበሩት የግዕዝ (Ethiopic) ፊደላት ለመጀመሪያ ጊዜ በኮምፕዩተር ተከተቡ። ሞዴት በመባል የታወቀውን የቃላት ማተሚያ የማይክሮሶፍትን ዶስ በመጠቀም በ፲፱፻፹ ዓ.ም. ኣሜሪካ
ውስጥ ለገበያ ኣቀረቡ። ግዕዝ በኮምፕዩተር እንዲከተብ የፈጠሩበትን ዘዴ በዩናይትድ
እስቴትስ ፓተንት መጠበቅ ቢችሉም በእዚያን ጊዜ ኢትዮጵያ የፓተንት ሕግ ስላልነበራት የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን ሕጉ ሲወጣ ጉዳዩ ይታያል በማለት ስለወሰነ [1] ፓተንት ኣልወጣለትም።
Click
the link below to listen Part I interview of the founder of Ethiopic software (
Geezedit), Dr.Abera Mola
0 comments:
Post a Comment