በዓመቱ መጀመሪያ በመስከረም ወር
2006 ዓ.ም ለ12 ዓመታት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት በመሆን ያገለገሉት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ፤ ከስልጣናቸው የወረዱ ሲሆን በቦታቸውም ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ተተክተዋል፡፡ በአምባሳደርነት ዘመናቸው የውጭ አገር ኢንቨስተሮችን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣትና አገር ውስጥ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ በማግባባት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸው የሚነገርላቸው ዶ/ር ሙላቱ፤ የፕሬዚዳንትነት ስልጣናቸውን ከተረከቡ በኋላም ሥራቸው በቤተመንግስት አካባቢ የተገደበ አልሆነም፡፡ በተለያዩ አገራት እየዞሩ የውጭ ኢንቨስተሮችን የማግባባት ሥራቸውን ቀጥለውበታል፡፡ በዓመቱ ከተከናወኑ አነጋጋሪ ጉዳዮች መካከል አንድነት ፓርቲ ከሰላማዊ ሰልፍ ጋር በተገናኘ የመብት ጥሰትና መጉላላት ተፈጽሞብኛል በማለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባንና የከተማዋን ፖሊስ ኮሚሽን በፍ/ቤት መክሰሱ ተጠቃሽ ነው፡፡ ፍ/ቤቱም ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ “ክሱ ለክስ የሚያበቃ ምክንያት የለውም፣ አስተዳደራዊ ውሣኔ ያገኝ የሚል ውሣኔ የሰጠ ሲሆን ፓርቲውም በጊዜው ይግባኝ እንደሚጠይቅ ገልፆ ይግባኝ ለመጠየቅ በሂደት ላይ ይገኛል፡፡ የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ እንዲሁም የኢዴፓ መስራችና ሊ/መንበር የነበሩት አቶ ሙሼ ሰሙ ራሳቸውን ከፖለቲካ ፓርቲ ያገለሉት በዚሁ ባሳለፍነው ዓመት ነው፡፡ ዶ/ር ነጋሶ ከጤና ጋር በተያያዘ፣ አቶ ሙሼ ደግሞ “የጥሞና ጊዜ እፈልጋለሁ” በሚል የፓርቲ ፖለቲካ በቃን ብለዋል፡; Click the link below to read more ...
Monday, September 8, 2014
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
0 comments:
Post a Comment