Sunday, February 9, 2014

የቀድሞ የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት ከአገር ኮበለሉ::

         

የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩትና በአሁኑ ሰዓት የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት የተከበሩ አቶ ኡመድ ኡባንግ፤ ከአገር መኮብለላቸውን ምንጮቻችን ገለፁ፡፡ አቶ ኡመድ ኡባንግ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ከሃገር መውጣታቸውን የጠቆሙት ምንጮች፤ ወደ ኢትዮጵያ እንደማይመለሱ ለሚቀርቧቸው ሰዎች መናገራቸውን አመልክተዋል። የሚኒስትር ዴኤታውን መኮብለል በተመለከተ የጠየቅናቸው የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር / ሽፈራው ተክለማርያም፤ አቶ ኡመድ በስራ ገበታቸው ላይ እንደሌሉ ማረጋገጣቸውን ገልፀው መስሪያ ቤታቸው ለተለየ ተልዕኮ እንዳላሰማራቸውና ፈቃድ ሳይጠይቁ ከስራ ገበታቸው እንደቀሩ ተናግረዋል፡፡ / መስሪያ ቤታቸው ጉዳዩን እያጣራ መሆኑንም አክለው ገልፀዋል፡፡ አቶ ኡመድ ከጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንትነት የተነሱት በክልል መንግስቱ የስራ አፈፃፀም ላይ ለአንድ ሳምንት ከዘለቀ ግምገማ በኋላ ሲሆን፤ ሌሎች የክልሉ ባለስልጣናትም በዚሁ ግምገማ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ይታወሳል፡፡  Source ( AddisAdmas) 

0 comments:

Post a Comment