When we read the news below
from Awra-amba times we were wondering
why anti-Corruption commission keep silent
(has an Elephant ear) on news of this nature. Isn't this the objective of the Anti-corruption
commission to investigate and look into the alleged case? Not long ago the
commission expressed its dissatisfaction over media out lets (both Government and
Private) that they are not to adequately report on corruption news as well as not
doing enough on investigative journalism.
Have your say!
አውራምባ
ታይምስ (አዲስ አበባ) – ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢህአዴግ መንግስትን ድክመት ፈልፍሎ በማውጣት፤ በተለይም በሃገሪቱ የተንሳራፋውን ሙስና በቁርጠኝነት በማጋለጥ በብቸኝነት ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ እንደሆነ የሚነገርለት “ኢትዮ- ምህዳር” ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ታሰረ፡፡
የኢትዮ ምህዳር ዋና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ጌታቸው ማሩ በዛሬው እለት ጥቅምት 26 ቀን 2006 ዓም ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ ለገጣፎ በሚባለው አካባቢ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ በተሰየመ ጊዚያዊ ችሎት እንዲቀርብ የተደረገ መሆኑ ታውቋል፡፡ ጋዜጠኛው በሥም ማጥፋት ወንጀል የተከሰሰ መሆኑም በደፈናው ተነግሮታል፡፡ ከሳሽ አቃቤ ሕግ የክሱን ዝርዝር ሳይገልፅ በጋዜጠኛ ጌታቸው ማሩ ላይ የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቆበታል፡፡
ጋዜጠኛው በታሰረበት ለገጣፎ አካባቢ ቋሚ ፍ/ቤት ባለመኖሩ ከሰንዳፋ ፍ/ቤት በተላከ አንድ ዳኛ ብቻ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ በተሰየመ ተዘዘዋሪ ችሎት ፊት የቀረበው የኢትዮ- ምህዳር ዋና አዘጋጅ ጌታቸው ማሩ በከሳሽ አቃቤ ሕግ ጥያቄ መሰረት ለ14 ቀን በእስር ቤት እንዲቆይ ትዕዛዝ መስጠቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ዛሬ ለ14 ቀን እስርቤት እንዲቆይ የተወሰነበት ጌታቸው ማሩ፤ በለገዳዲ – ለገጣፎ ሲታሰር ሁለተኛው የኢትዮ ምህዳር ጋዜጠኛ መሆኑ ነው፡፡ ከቀናቶች በፊት የጋዜጣዋ ሥራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ሚሊዮን ደግነው ሲቪልና የፖሊስ ልብስ በለበሱ አራት ሰዎች በለገዳዲ ለገጣፎ እንዲታሰር መደረጉ የሚታወቅ ሲሆን የጋዜጣዋ ከፍተኛ አዘጋጅ የሆነው ኤፍሬም በየነም ጋዜጣዋ ካቀረበችው ዘገባ ጋር ተያይዞ ክስ ለመከታተል ከባልደረቦቹ ጋር ወደ አዋሳ በሄደበት ወቅት ጥቅምት 20 ቀን 2006 ዓ.ም አደጋ ደርሶበት በአከርካሪ አጥንቱና ሳምባው ላይ ጉዳት ደርሶበት በአዲስ አበባ ኮሪያ ሆስፒታል ህክምናውን በመከታተል ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡
ኢትዮ-ምህዳር ጋዜጣ በለገዳዴ-ለገጣፎ አካባቢ የሚካሄደውን ምዝበራና ሙስና በተከታታይ ያጋለጠች ሲሆን ዛሬ 14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀበት ጋዜጠኛ ጌታቸው ማሩም ሆነ ከሁለት ቀናት በፊት በፖሊስ ተይዞ እዚያው እስር ቤት የሚገኘው ስራ አስኪያጁ ሚሊዮን ደግነው፣ በደፈናው ስም ማጥፋት ወንጀል ይከሰሱ እንጂ ጉዳዩ ከዚያም በላይ የሆነ የክልሉ መንግስት ሴራን በማጋለጣቸው ለእስር እንደተዳረጉ ለጋዜጠኞቹ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ይገልጻሉ፡፡
እነዚህ ወገኖች እንደሚሉት የቀድሞው የከተማዋ ከንቲባ የሆኑት አቶ መገርሳ ገለታ በሙስና ወንጀል ተከሰው ስምንት አመት እስራት ከተፈረደባቸው በኋላ በሁለት ወራት እስራት ብቻ ተለቀው በሌላ ከፍተኛ ኃላፊነት መመደባቸውን ጋዜጣዋ በማጋለጧ ጉዳዩን ማድበስበስ የፈለጉ ወገኖች የወሰዱት አጸፋዊ እርምጃ ሊሆን እንደሚችልም ግምታቸውን ሰጥተዋል፡፡ የአቶ መገርሳ ጉዳይ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስታዊ ምክርቤት ሳይቀር የውይይት አጀንዳ እንደነበርም የአውራምባ ታይምስ ምንጮች ይገልጻሉ፡፡

0 comments:
Post a Comment