Friday, January 14, 2011

አሜሪካዊው በጸጥታ አስከባሪዎች በተተኮሰ ጥይት ተገደለ::

የገና በዓልን ከቤተሰቦቹ ጋር ለማክበር ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ የነበረው ትውልደ ኢትዮጵያዊው አሜሪካዊ ወጣት አረፈዓይኔ ቦብ ዊን ከፖሊስ በተተኮሰ ጥይት ሕይወቱ ማለፉን ባገር ውስጥ እየታተመ የሚወጣው የሪፖርትር ጋዜጣ ገለጸ: ከተገኘው ዜና መረዳት እንደታቸለው ሟች አረፈ አይኔ የ20 አመት ወጣትና ባሜሪካ በካልፎሪኒያ ክፍለ ግዛት ሳንሆሴ ከተማ በሚገኝ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ውስጥ የሁሉተኛ አመት የኮሌጅ ተማሪ የነበረ ሲሆን አያት ሆሲፒታል በሚገኝ የምሽት ክበብ ውስጥ ከቤተሰቦቹ ጋር በሚዝናናበት ወቅት ረብሻ ሲፈጠር መዝናናታቸውን አቁመው በመውጣት በያዙት ተሽከርካሪ ለመጓዝ ሲንቀሳቀሱ፣ ፖሊስ ደርሶ ‹‹ቁሙ›› ሲላቸው ዝም ብለው ሲሄዱ የተኩስ ድምፅ እንደሰሙ ና በተተኮሰው ጥይት ሟች አረፈ አይኔ ግራ ጎኑን እንደተመታ ቤተሰቦቹ ያስረዳሉ:: ዝርዝሩን ለማንበብ እቺን ይጫኑ::

0 comments:

Post a Comment