
ገና ጾምን ምክንያት በማድረግ ለጻሚ ተማሪዎች በየአመቱ ሲደረግ የነበረው የጾም መግደፊያ ዝግጅት በዚህ አመት ባለመደረጉ ባዲስ አበባ ዪነቨርስቲ በሳይንስ ፋኩልቲ ረብሻ ተቀስቅሶ እንደነበር በሀገር ውስጥ የሚተታመው የሪፖርተር ጋዜጣ ገለጸ:: ተማሪዎቹ ተቃውሟቸውን የረሀብ አድማ በማድረግ ያሳዩ እንጂ በሚቀጥለው ቀን ወደ ምግብ መመገቢያው ካፌ በሚሄዱ ተማሪዎች ላይ ቁጣቸውን ድንጋይ በመወወርወር አሳይተዋል ሲል ጋዜጣው ይገልጻል:: በጥናት ላይ እንደነበረች በተወረወረ ድንጋይ የቤተ መጻሕፍቱ ሕንፃ መስታወት ሲሰበር በማየቷ በድንጋጤ በሥላሴ ቤተክርስቲያን በኩል ባለው በር ሮጣ ማምለጧን አንዲት ተማሪ ትናገራለች::
ዝርዝሩን ያንብቡ::
0 comments:
Post a Comment