Monday, December 27, 2010

ኣርቲስት ሃመልማል ኣባተ በቢሮክራሲው በመማረሯ ኣዲስ ዜማ ልትለቅ ነው ።

በማታውቀውና የከተማውን ማስተር ፕላን ባልጠበቀ ሁኔታ ለአንድ ግለሰብ ከፊት ለፊቷ ያለው ቦታ ተሰጥቶ ሕንፃ መገንባቱን የገለጸችው አርቲስት ሐመልማል፤ የአካባቢው ነዋሪዎች ፍሳሽ የሚወገድበት ቱቦ በመዘጋቱ ያለፉትን ሁለትና ሦስት ክረምቶች ጐርፍ በቤታቸው ውስጥ እየገባ ማሳለፋቸውን ተናግራለች፡፡ ‹‹ውኃ ወደ ላይ አይፈስም›› የምትለው አርቲስቷ፣ ‹‹ለውጥ ነው›› በሚል የተሠራው የፍሳሽ ማስወገጃ የሚያስገርምና ሕግና ሥርዓት ባለበት አገር የማይፈጸም ሥራ መሆኑን ጠቁማለች፡፡ ችግሩ በጣም ስለበዛባቸው የሠፈሩ ሽማግሌዎች በመሰብሰብ ቀበሌ፣ ክፍለ ከተማ፣ ማዘጋጃ ቤትና ኢሕአዴግ ጽ/ቤት ድረስ ቢሄዱም፣ አንዱ በአንዱ ላይ ከማሳበብ የዘለለ ውሳኔ አለማግኘታቸውን ሐመልማል ገልጻለች፡፡ በቢሮክራሲው የተማረረችው ኣርቲስት ሃመልማል ኣባተ በዚህም የተነሳ ነጻ ዜማ ልትለቅ ነው። ተጨማሪ ያንብቡ>>>

0 comments:

Post a Comment