Sunday, October 10, 2010

መለስ ዜናዊ የስኴር ኮርፕሬሽንና ኢንጂነሪንግ ኮርፕሬሽን በኔ ትእዛዝ ስር ይሁን አሉ::

የስኳርና የኢነርጂ ዘርፎች በቀጣዩ አምስት ዓመታት ግዙፍ ግንባታ የሚካሄድባቸው በመሆናቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርበት ጉዳዩን መከታተል በመፈለጋቸው ነው በማለት ያስረዳሉ፡፡ በእርግጥ ስኳርን በሚመለከት ሦስቱ ስኳር ፋብሪካዎች የሚያካሂዱት የማስፋፊያ ፐሮጀክቶች አዲስ ከሚገነባው የተንዳሆ ስኳር ጋር ተዳምሮ የፋብሪካ ግንባታና አሁን ካለው 314.5 ሺሕ ቶን ስኳር በ2007 ከሰባት እጥፍ በላይ በማሳደግ ወደ 2.2 ሚሊዮን ቶን የማድረስ ዕቅድ አለ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ሦስት አዳዲስ የስኳር ፋብሪካዎች ይገነባሉ፡፡ ኢነርጅን በሚመለከትም አሁን ካለው ሁለት ሺሕ ሜጋ ዋት ከአምስት ዓመት በኋላ እስከ ስምንት ሺሕ ሜጋ ዋት የሚደርስ ኃይል ለማመንጨት የሚያስችሉ ግንባታዎች ለማካሄድ ታቅዷል፡፡ በሁለቱ ተቋማት የሚካሄደው ግንባታ ግን በዋናነት የሚቀናጀው አዲስ በተቋቋመው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን አማካኝነት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ለኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽኑ ብርጋዴል ጀነራል ክንፈ ዳኘውን ሹመዋል፡፡ በብርጋዴር ጄነራሉ የሚመራው አዲሱ ኮርፖሬሽንም ተጠሪነቱም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ነው፡፡ በዚህ ኮርፖሬሽን አማካኝት ለሚካሄዱ የፋብሪካ ግንባታም ሆኑ ለኃይል ማመንጫ ግንባታዎች የሚያስፈልጉ ምርቶች ኮርፖሬሽኑ አገር ውስጥ እንዲመረት ያደርጋል፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ...>>>

0 comments:

Post a Comment