Saturday, July 3, 2010

አለም አቀፍ የሊስትሮዎች ቀን በታላቅ ድምቀት ተከበረ::

ባለም ዙሪያ ላሉ ሊስትሮች ክብር ለመስጠት ተብሎ በተደረገው በዚሁ ደማቅ ዝግጅት ላይ ከ 1000 በላይ ሊስትሮች እንደትገኙ ለማወቅ ተችሏል:: ከዝህም በተጨማሪ ከጀርመን ሊስትሮች ጋር ያለውን የአላማና የትግል አንድነት ለመግለጽ አምስት ሺ አሮጌ የሊስትሮ ሳጥኖች ከኢትዮጵያ ወደ ጀርመን እንዲላኩ የተወሰነ ሲሆን እንደ ማህበሩ ፕሬዝዳንት የተከበሩ አቶ ያሬድ ገ/ስላሴ ገለጻ የሊስትሮቹ ሳጥኖች በበርሊን ከተማ ውስጥ ለሁለት ሳምንት ያህል የጫማ ማጽዳት ስራ ይካሄድባቸዋል:: በስነ-ስርአቱ ላይ ከኬንያ " ኪዊ" ቀለም ፋብሪካ የመጡ ተወካዮች የተገኙ ሲሆን አጋርነታቸውን ለመግለጽ ለሊስትሮቹ አንድ አንድ ኪዊ ቀለም ለግሰዋል:: ተጨማሪ ያንብቡ>>>

0 comments:

Post a Comment