
የመኢአድ ፕሬዝዳንት ኢንጂነር ሀይሉ ሻውል በቅርቡ ፓርቲአቸው የደረሰበት ሽንፈት እንዳበሳጫቸውና በዚሁ ምክንያት ከፖሎቲካው አለም መሰናበታቸውን ኢትዮ ቻናል የሚባል ሀገር በቀል ጋዜጣ ላንባቢዎቹ አቀረበ:: " ፖሎቲካው በቃኝ የሚያሳስበኝ እኔን የሚተካኝ አለማግኘቴ ነው" ብለዋል ኢንጂነሩ:: ይሄን አባባላቸውን የቅርብ ሰዎቻቸው የተስማሙበት አይመስልም:: ከዜናው መረዳት እንደተቻለው የአመራር አካላቱ ለመሪነት ራሳቸውን እያጩ ይገኛሉ:: በዚህም መሰረት የድርጅት ጉዳይ ሀላፊውና የዶክተር ሰናይ ልኬ ወንድም የሆኑት አቶ ያእቆብ ልኬ ባንድ በኩል ሻለቃ መንግስቴ በሌላኛው ጠርዝ ከሀገረ አሜሪካ ደግሞ አቶ አባይነህ ብርሀኑ ገመድ ጉተታ መጀማመራቸውን ዜናው ያስረዳል:: ከቡልቻ ደመቅሳ ቀጥሎ ፖሎቲካ በቃኝ ሲሉ ኢንጂነር ሀይሉ ሁለተኛው አንጋፋ ፖሎቲከኛ መሆናቸው ነው:: ቡዙዎች ማነህ ባለ ተራ ..? ይላሉ ::
ምንጭ
0 comments:
Post a Comment